ባለረዥም ጭራ ጦጣ ስፓይደር ጦጣ (Spider Monkey) ይባላል፡፡ ስፓይደር ጦጣዎች ከጭራቸው በተጨማሪ እጆቻቸውም ረዣዥሞች ናቸው፡፡ 

​በመንጋ የሚኖሩት የሜዳ አህዮች ሦስት ዝርያ አላቸው፡፡ ከሌሎች እንስሳት በተለየ መልኩ በነጭና ጥቁር መስመር ባሸበረቀ ቆዳቸው ይታወቃሉ፡፡ 

​በመርዛማነታቸው የሚታወቁት ኮብራ እባቦች ‹‹ንጉሥ ኮብራ›› በመባልም ይታወቃሉ፡፡ በብዛት የሚገኙት በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ እስያ ነው፡፡ 

​አናኮንዳ በዓለም በክብደታቸው ትልቅነት ከሚታወቁት የእባብ ዓይነቶች ቀዳሚው ነው፡፡ ሲወለድ ቁመቱ አንድ ሜትር ሲሆን፣ ሲያድግ እስከ 8.6 ሜትር ድረስ ይረዝማል፡፡

​ጉማሬ ባብዛኛው ውኃ ውስጥ በመኖር ይታወቃል፡፡ ሰውነቱን ሙሉ ለሙሉ ውኃ ውስጥ ዘፍቆ ለ15 ደቂቃ ያህል መቆየትም ይችላል፡፡

​ጭልፊት በኢትዮጵያ ተረትና ምሳሌ ውስጥ ትታወቃለች፡፡ በመዝገበ ቃላዊ ፍቺዋ ዶሮን፣ ሥጋና ዓሣ የምትነጥቅ አሞራ፣ በሐምሌና በነሐሴ ወራት የማትታይ ይላታል፡፡ 

Pages