የ12ኛ ምእት ዓመቱ ይምርሀነ ክርስቶስ ውቅር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን ጥንታዊ ሥዕሎችን ለመጠገንና እንዲሁም ያሉበትን ልዩ ልዩ ችግሮች ለማጥናት የሚውል 31.8 ሚሊዮን ብር (150,000 ዶላር)  ከአሜሪካ አምባሳደር ፈንድ (Ambassador`s Fund for Cultural Preservation Award) ተገኘ፡፡ ለፕሮጀክቱ አፈጻጸም ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) ከዓለም የቅርስ ልማት ፈንድ ጋር ዓርብ የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የስምምነት ፊርማ አድርጓል፡፡

በአገሪቱ የተከሰተው ድርቅ እንደ ሌሎች አካባቢዎች ሁሉ በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክም ክንዱን አሳርፏል፡፡ በፓርኩ፣ ወትሮውንም ቢሆን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደሮችና ከርቀት የሚመጡትም ራሳቸውንና የቤት እንስሳቸውን በሕይወት ለማቆየት በሺሕ የሚቆጠሩ እንስሳት ሲያሰማሩበት 

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ከሚታወቁ ዝነኛ ሰዎች ተቀዳሚው ናቸው፡፡ አገርን መምራት፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች መሳተፍ፣ ቤተሰብን ማስተዳደርና ሌሎችም ብዙ ኃላፊነቶች የተደራረቡባቸው ፕሬዚዳንቱ፣ ባሉበት ቦታ ሆነው ዘወትር ስፖርት እንደሚሠሩ በርካታ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ አበባን ጨምሮ ከሚገኙበት አካባቢ ውጭ የርቀት ትምህርት እንዳይሰጡ መመሪያ መተላለፉን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡

​ዋና ከረዥም ዘመናት በፊት የተጀመረ ስፖርት ቢሆንም፣ ብዙ ሳይለመድ ቆይቷል፡፡ ቀስ በቀስ እየተለመደ ሲመጣ ግን እንደ አንድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በብዙዎች ይዘወተር ጀመረ፡፡ 

Pages