ፍሬ ከናፍር

‹‹ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ የተጠለፉ ሕፃናትና ሴቶች እንዲለቀቁ ጽኑ ጥረት ይደረግ!››

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ፣ በጋምቤላ ክልል ጃካዋ አካባቢ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. አፍነው የወሰዷቸው ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ፣ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ድረ ገጽ በኩል ያስተላለፉት ማሳሰቢያ፡፡ ዓርብ ሌሊት በኑዌርና አኙዋ ተወላጆች ላይ ጥቃት የሰነዘሩት የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት 208 ንጹሐን ዜጎችን ገድለው፣ 108 ሕፃናትንና ሴቶች መጥለፋቸው ታውቋል፡፡ የደቡብ ሱዳኖቹ ሙርሌዎች እንዲህ ያለውን ጥቃት ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ በመጋቢት ወር ከጋምቤላ 26 ንጹሐንን ገድለው፣ ከብቶቻቸውን ዘርፈው የሄዱበት የሚታወስ ነው፡፡